አዲስ አበባ፣ ሰኔ 1፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) የአማራ ክልል ርዕሰ መስተዳደር አረጋ ከበደ እና የግብርና ሚኒስትር ግርማ አመንቴ (ዶ/ር) በአዲስ አበባ የተገነቡ የልማት ስራዎችን ጎብኝተዋል፡፡
በጉብኝታቸውም ፥ የለሚ ኩራ የግብርና ምርት መሸጫ ማእከል፣ የእንስሳት ልማት እና ልህቀት ማእከል፣ ለነገዋ የሴቶች ተሃድሶና ማበልጸጊያ ማእከል እንዲሁም ሌሎች የልማት ስራዎችን ተመልክተዋል፡፡
በአዲስ አበባ የተከናወኑ የልማት ስራዎች እና ታላላቅ ፕሮጀክቶች የህብረተሰቡን ተጠቃሚነት የሚያረጋግጡና ለሌሎች ክልሎችም ተሞክሮ መሆናቸውን ርእሰ መስተዳድር አረጋ ተናግረዋል፡፡
አክለውም ፥ በተለያዩ ክፍለከተሞች የተገነቡት የልማት ስራዎች ዝቅተኛ የህብረተሰብ ክፍሎችን ተጠቃሚ የሚያደርጉና የኑሮ ውድነቱን የሚያቃልሉ እንደሆኑ መግለጻቸውን ከከንቲባ ጽህፈት ቤት ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡