Site icon Welcome to Fana Broadcasting Corporate S.C

ሃይል ተቋርጦባቸው የነበሩ የወለጋ ዞን ከተሞች ዳግም የአገልግሎቱ ተጠቃሚ ሆኑ

አዲስ አበባ፣ ሰኔ 1፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) በኦሮሚያ ክልል አራቱም የወለጋ ዞኖች በነበረው የፀጥታ ችግር ምክንያት የኤሌክትሪክ ሃይል ተቋርጦባቸው የነበሩ የገጠር ከተሞች ዳግም የአገልግሎቱ ተጠቃሚ ሆነዋል፡፡

በዞኖቹ በነበረው የፀጥታ ችግር ሳቢያ በደረሰ የኤሌክትሪክ መሰረተ-ልማት ውድመት ሃይል ተቋርጦባቸው የነበሩ የገጠር ከተሞች በተሰራ የጥገና ሥራ ነው ዳግም የአገልግሎቱ ተጠቃሚ የሆኑት፡፡

በዚህ መሰረትም በምዕራብ ወለጋ ዞን የዶንጎሮ ጌቦ፣ ዶንጎሮ ዲስ፣ ሆታሎ ቴሌኮም ሳይት እና የካለይ የውሃ አቅርቦት ዳግም የአገልግሎቱ ተጠቃሚ መሆናቸውን የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት አስታውቋል፡፡

በተመሳሳይ በምስራቅ ወለጋ ዞን የሃሮ ፎላ ቴሌኮም፣ መንደር 8፣ ኤፈሬም፣ ጉቤ እና መንደር 15 አገልግሎቱን ዳግም ማግኝት መቻላቸው ተጠቁሟል፡፡

በተጨማሪም በሆሮ ጉዱሩ ዞን ስር የሚገኙት የገንቦ ስላሴ ቴሌኮም እና ኡታልቾ የህዝብ ማዕከል ተቋርጦ የነበረው አገልግሎት ዳግም መመለሱ ነው የተገለጸው፡፡፡

በቀጣይ በሌሎች አካባቢዎች የወደሙ የኤሌክትሪክ መሰረተ ልማቶችን በመጠገን የአካባቢው ማህበረሰብ ዳግም የአገልግሎቱ ተጠቃሚ እንዲሆን እየተሰራ ነው መባሉንም የአገልግሎቱ መረጃ ያመላክታል፡፡

Exit mobile version