አዲስ አበባ፣ ግንቦት 30፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) በብልፅግና ፓርቲ የኦሮሚያ ክልል ቅርንጫፍ ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ ፍቃዱ ተሰማ እና የአፋር ክልል ም/ርዕሰ መስተዳድር አቶ ኤሌማ አብበከርን ጨምሮ ከፍተኛ የስራ ሃላፊዎች በወላይታ ሶዶ ከተማ የተለያዩ የልማት ስራዎችን እየጎበኙ ይገኛሉ።
ከፍተኛ አመራሮቹ በከተማው የሌማት ትሩፋት፣ ሌሎች የግብርና ልማት ስራዎችን እንዲሁም በከተማው እየተከናወኑ ያሉ ሌሎች የልማት ስራዎችን ተዘዋውረው በመጎብኘት ላይ ናቸው።
በጉብኝቱ የወላይታ ዞን የመንግስት ረዳት ተጠሪ አቶ ተመስገን አለማየሁ እና የከተማው ከንቲባ አቶ ጀገና አይዛን ጨምሮ ሌሎች ከፍተኛ አመራሮችም ተሳትፈዋል።
በታሪክነሽ ሴታ