አዲስ አበባ፣ ግንቦት 29፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) የእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ ክለቦች በቪዲዮ የተደገፈ ዳኝነት (ቫር) በሚቀጥለው የውድድር ዘመንም ሥራ ላይ መዋሉ እንዲቀጥል ወሰኑ፡፡
የእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ 20 ክለቦች ቫር ሥራ ላይ መዋሉ ‘‘ይቀጥል ወይስ ይቋረጥ?’’ በሚል ሀሳብ ላይ ድምጽ ሰጥተዋል፡፡
በዚሁ መሰረት 19ኙ ክለቦች ቫር ሥራ ላይ መዋሉን እንዲቀጥል ሲስማሙ ዎልቨር ሃምፕተን ግን ተቃውሟል፡፡
ቫር እንዲሰረዝ ከ20 የፕሪምየር ሊግ ክለቦች 14ቱ መቃወም ነበረባቸው መባሉን የዘገበው ቢቢሲ ነው።