Site icon Welcome to Fana Broadcasting Corporate S.C

በመድረኮች የተሰጡ ግብዓቶችን በዕቅድ አካተን እየሠራን ነው- አቶ እንዳሻው ጣሰው

አዲስ አበባ፣ ግንቦት 29፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) በክልሉ በተካሄዱ ሕዝባዊ ውይይቶች የተሰጡ ግብዓቶችን የዕቅድ አካል አድርገን እየሠራን ነው ሲሉ የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ርዕሰ መሥተዳድር እንዳሻው ጣሰው ገለጹ፡፡

አቶ እንዳሻው ከሀዲያ ዞን የሀገር ሽማግሌዎች ጋር በሠላምና ልማት ዙሪያ ባደረጉት ውይይት ላይ እንዳሉት÷ በክልሉ በተካሄዱ ሕዝባዊ ውይይቶች የተነሱ የሕዝብ ጥያቄዎች እና ግብዓቶች የዕቅድ አካል በማድረግ ጥያቄዎችን ለመመለስ በትኩረት እየተሠራ ነው፡፡

በዚህም የክልል አመራርን የማደራጀት፣ የዞን፣ ልዩ ወረዳ እና የወረዳ አመራርን የማጠናከር ሥራ መከናወኑን አብራርተዋል፡፡

የግብርና ሥራው ወቅቱን ጠብቆ እንዲቀጥል መሠራቱን ጠቅሰው በቂ የአፈር ማዳበሪያ ለአርሶ አደሩ ቀርቧል ማለታቸውን የክልሉ ኮሙኒኬሽን መረጃ አመላክቷል፡፡

በሁሉም ከተሞች የገቢ አሰባሰብ እና የመሰረተ-ልማት ሥራዎች ሳይቋረጡ እንዲቀጥሉ ማድረግ መቻሉን ገልጸው÷ የኢንቨስትመንት ቦታዎችን በአግባቡ ማስተላለፍ መቻሉን እና ሌሎች ተግባራትም መከናወናቸውን አስረድተዋል፡፡

Exit mobile version