የሀገር ውስጥ ዜና

ኢትዮጵያ እና ሲንጋፖር ትራንስፖርትን ጨምሮ በተለያዩ ዘርፎች በጋራ ለመስራት ተስማሙ

By Amele Demsew

June 06, 2024

አዲስ አበባ፣ ግንቦት 29፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) የኢትዮጵያ እና የሲንጋፖር መንግሥታት በትራንስፖርትና ሌሎች የሁለትዮሽ ጉዳዮች ላይ በጋራ ለመሥራት የሚያስችላቸውን ስምምነት መፈረማቸውን የጠቅላይ ሚኒስትር ጽሕፈት ቤት አስታወቀ፡፡

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) በሲንጋፖር ሪፐብሊክ ኢስታና ቤተመንግስት በነበራቸው ቆይታ÷ የሁለቱ ሀገራት መሪዎች በተገኙበት በሁለትዮሽ ምክክር ላይ የመግባቢያ ስምምነት ተደርጓል፡፡

በተጨማሪም በኢፌዴሪ ትራንስፖርት እና ሎጂስቲክስ ሚኒስቴር እና በሲንጋፖር የትራንስፖርት ሚኒስቴር መካከል የፍላጎት ስምምነት መፈረሙን የጠቅላይ ሚኒስትር ጽሕፈት ቤት መረጃ አመላክቷል፡፡