አዲስ አበባ፣ ግንቦት 29፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) የኢትዮጵያ እና የሲንጋፖር መንግሥታት በትራንስፖርትና ሌሎች የሁለትዮሽ ጉዳዮች ላይ በጋራ ለመሥራት የሚያስችላቸውን ስምምነት መፈረማቸውን የጠቅላይ ሚኒስትር ጽሕፈት ቤት አስታወቀ፡፡
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) በሲንጋፖር ሪፐብሊክ ኢስታና ቤተመንግስት በነበራቸው ቆይታ÷ የሁለቱ ሀገራት መሪዎች በተገኙበት በሁለትዮሽ ምክክር ላይ የመግባቢያ ስምምነት ተደርጓል፡፡
በተጨማሪም በኢፌዴሪ ትራንስፖርት እና ሎጂስቲክስ ሚኒስቴር እና በሲንጋፖር የትራንስፖርት ሚኒስቴር መካከል የፍላጎት ስምምነት መፈረሙን የጠቅላይ ሚኒስትር ጽሕፈት ቤት መረጃ አመላክቷል፡፡