Site icon Welcome to Fana Broadcasting Corporate S.C

በጉምሩክ ኮሚሽን ሐዋሳ ቅርንጫፍ 1 ነጥብ 4 ቢሊየን ብር ዋጋ ያላቸው የኮንትሮባንድ ዕቃዎች መያዙን ገለጸ

አዲስ አበባ፣ ግንቦት 28፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) ባለፉት አሥር ወራት 1 ነጥብ 4 ቢሊየን ብር ዋጋ ያላቸው የኮንትሮባንድ ዕቃዎች መያዙን በጉምሩክ ኮሚሽን የሐዋሳ ቅርንጫፍ ጽሕፈት ቤት አስታወቀ፡፡

ከተያዙት ዕቃዎች መካከልም÷ አልባሳት፣ የተለያዩ ሀገራት ገንዘቦች፣ የመዋቢያ ዕቃዎች፣ ኤሌክትሮኒክስ፣ ነዳጅ፣ የምግብ ዘይት፣ መድኃኒትና አደንዛዥ ዕፆች እንደሚገኙበት የጽሕፈት ቤቱ ሥራ አስኪያጅ ታደሰ መርዕድ ተናገረዋል።

ለዕቃዎቹ መያዝ የሕብረተሰቡ ሚና ከፍተኛ መሆኑን ገልጸው በቀጣይም ትብብሩ እንዲቀጥል ጠይቀዋል፡፡

የሲዳማ ክልል የፀጥታ ቢሮ ኃላፊ ዓለማየሁ ጢሞቲዮስ በበኩላቸው÷ የኮንትሮባንድ ንግድ መንግሥትና ሕዝብን የሚጎዳ መሆኑን መገንዘብ ይገባል ብለዋል፡፡

አንዳንድ የፀጥታ አካላት ጉዳዩን የጉምሩክ ኮሚሽንና የፌዴራል ፖሊስ ሥራ ብቻ አድርገው ማየታቸውም ኮንትሮባንድን በመከላከል ሂደት እያጋጠመ ያለ ችግር መሆኑን ነው ያመላከቱት፡፡

በጥላሁን ይልማ

Exit mobile version