Site icon Welcome to Fana Broadcasting Corporate S.C

በሕንድ በከባድ ሙቀት ምክንያት የ56 ሰዎች ሕይወት አለፈ

አዲስ አበባ፣ ግንቦት 27፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) በሕንድ ከፈረንጆቹ መጋቢት እስከ ግንቦት ድረስ ባጋጠመ ከባድ ሙቀት ምክንያት የ56 ሰዎች ሕይወት ሲያልፍ 25 ሺህ ያህሉ ለጤና ዕክል መዳረጋቸው ተሰምቷል፡፡

ከአጠቃላይ ሟቾች መካከል የ46ቱ ሕይወት ያለፈው በግንቦት ወር ብቻ መሆኑን ሂንዱስታን ታይምስ ጋዜጣን ጠቅሶ ሲጂቲኤን ዘግቧል፡፡

በሌላ በኩል በሕንድ ከፈረንጆቹ መጋቢት 1 እስከ አሁን 24 ሺህ 849 ሰዎች ከሙቀት መጨመር ጋር በተያያዘ የጤና ዕክል እንዳገጠማቸው ዘገባው አመላክቷል፡፡

በዚህ ዓመት ሕንድ ከባድ የሙቀት መጠን እንዳጋጠማት የተገለጸ ሲሆን÷ ለአብነትም በተለያዩ አካባቢዎች ከ45 እስከ ከ50 ዲግሪ ሴልሺየስ በላይ የሆነ የሙቀት መጠን መመዘገቡ ተጠቅሷል፡፡

Exit mobile version