አዲስ አበባ፣ ግንቦት 27፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) የጃፓን መንግሥት ኢትዮጵያ ለምታከናውነው የቀድሞ ታጣቂዎችን ትጥቅ ማስፈታት እና መልሶ ማቋቋም ተግባር የሚውል 6 ነጥብ 7 ሚሊየን ዶላር ድጋፍ አደረገ፡፡
ድጋፉ የብሔራዊ ተሃድሶ ኮሚሽን የቀድሞ ታጣቂዎችን ትጥቅ ማስፈታትን ጨምሮ ከመልሶ ማቋቋም ጋር በተያያዘ ለሚያከናውናቸው ተግባራት ማስፈጸሚያ እንደሚውል ተገልጿል፡፡
ኮሚሽኑ በኢትዮጵያ ስምንት ክልሎች የቀድሞ ታጣቂዎችን ትጥቅ ማስፈታት እና መልሶ የማቋቋም ሥራ እንደሚያከናውን መገለጹን የገንዘብ ሚኒስቴር መረጃ አመላክቷል፡፡
የገንዘብ ድጋፉን ለማድረግ በተከናወነው የፊርማ ሥነ-ሥርዓት ላይ የገንዘብ ሚኒስትር ዴዔታ ሰመሪታ ሰዋሰው፣ የብሔራዊ ተሃድሶ ኮሚሽን ምክትል ኮሚሽነር ተስፋለም ይህደጎ፣ በኢትዮጵያ የጃፓን አምባሳደር ሺባታ ሂሮኖሪ እና የዩ ኤን ዲ ፒ የኢትዮጵያ ተወካይ ሳሙኤል ጂ ዶ ተገኝተዋል፡፡