ስፓርት

የፕሪሚየር ሊጉ ቀሪ ጨዋታዎች በሐዋሳ እንደሚካሄዱ ተመላከተ

By Tamrat Bishaw

June 03, 2024

አዲስ አበባ፣ ግንቦት 26፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ ከ27 እስከ 30ኛ ሣምንት ያሉ ጨዋታዎች በሐዋሳ ዩኒቨርሲቲ ስታዲየም መካሄዳቸው እንደሚቀጥል ተገለጸ፡፡

የኢትዮጵያ ፕሪሚየርሊግ አክሲዮን ማኅበር እንዳስታወቀው÷ ከኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን የዓለም ዋንጫ ማጣሪያ መልስ የፕሪሚየር ሊጉ የ27ኛ ሣምንት ጨዋታዎች ሐሙስ ሰኔ 6 ቀን 2016 ይጀምራሉ፡፡

ከ27ኛ ሣምንት ጀምሮ እስከ 30ኛ ሣምንት ያሉ ጨዋታዎችም በሐዋሳ ዩኒቨርሲቲ ስታዲየም መካሄዳቸውን እንደሚቀጥሉ ማኅበሩ አረጋግጧል፡፡