Site icon Welcome to Fana Broadcasting Corporate S.C

በፖርቹጋል የአየር ትርዒት ላይ በተፈጠረ ግጭት አንድ ፓይለት መሞቱ ተገለፀ

አዲስ አበባ፣ ግንቦት 26፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) በፖርቹጋል የአየር ትርዒት ላይ በተፈጠረ ግጭት የስፔን ዜግነት ያለው ፓይለት ህይወቱ ማለፉን የፖርቹጋል አየር ሀይል አስታውቋል፡፡

እንደ አየር ሀይሉ መረጃ÷ ከፖርቹጋል መዲና ሊዝበን ከተማ በ178 ኪሎ ሜትር ርቀት ላይ በምተገኘው የቤጃ ከተማ ላይ እየተካሄደ በነበረው የአየር ትርዒት ላይ አውሮፕላኖች ተጋጭተው አደጋ ተከስቷል፡፡

በግጭቱ አንደኛው አውሮፕላን ከቤጃ አየር ማረፊያ ክልል ውጭ ሲከሰከስ ሌላኛው አውሮፕላን ደግሞ በአየር ማረፊያው አቅራቢያ መከስከሱ ተገልጿል፡፡

በአደጋው አንድ ፓይለት ህይወቱ ሲያልፍ ሌላኛው ፖርቹጋላዊ ፓይለት ክፉኛ ተጎድቶ ወደ ቤጃ ሆስፒታል መግባቱ ነው የተገለፀው፡፡

የፖርቹጋል አየር ሀይል በተፈጠረው ክስተት ማዘኑን ገልፆ በአደጋው ሕይዎቱን ላጣው አብራሪ ቤተሰቦች መፅናናትን ተመኝቷል፡፡

አደጋውን ተከትሎ በስፔን እና ፖርቹጋል ኤሮቦቲክ ቡድኖች ሲካሄድ የነበረው የአየር ላይ ትርኢት እንዲቋረጥ መደረጉን ዩ ፒ አይ ዘግቧል፡፡

Exit mobile version