ስፓርት

ኤንዞ ማሬስካ የቼልሲ አሰልጣኝ ሆነ

By Mikias Ayele

June 03, 2024

አዲስ አበባ፣ ግንቦት 26፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) የ44 ዓመቱ ጣልያናዊው አሰልጣኝ ኤንዞ ማሬስካ ቼልሲን በዋና አሰልጣኝነት ለመምራት በይፋ ፊርማውን አስቀምጧል፡፡

ተሰናባቹን አሰልጣኝ ሞሪሲዮ ፖቼቲኖ ተክቶ እስከ ፈረንጆቹ 2029 የምዕራብ ለንደኑን ክለብ ለማሰልጠን ለፈረመው ማሬስካ ዝውውር ቸልሲ 10 ሚሊየን ዩሮ እንደሚከፍል ተገልጿል፡፡

ከዝውውሩ ጋር የተያያዙ ሠነዶች የተጠናቀቁ ሲሆን÷ ክለቡም ዛሬ መግለጫ እንደሚሰጥ ይጠበቃል ተብሏል፡፡

አሰልጣኝ ኤንዞ ማሬስካ ከሌስተር ሲቲ ጋር ባሳለፈው ስኬታማ ጊዜ ክለቡን ከሻምፒየን ሽፕ ወደ እንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ ማሳደግ ችሏል፡፡