የሀገር ውስጥ ዜና

በኦሮሚያ ክልል የሚንቀሳቀሱ የፖለቲካ ፓርቲዎች ከክልሉ መንግስት የስራ ሃላፊዎች ጋር እየተወያዩ ነው

By Amele Demsew

June 02, 2024

አዲስ አበባ፣ ግንቦት 25፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) በኦሮሚያ ክልል የሚንቀሳቀሱ የፖለቲካ ፓርቲዎች ከክልሉ መንግስት የስራ ሃላፊዎች ጋር በወቅታዊ ጉዳይ ዙሪያ እየተወያዩ ነው።

ውይይቱ የኦሮሚያ ክልል ርዕሰ መስተዳድር ሽመልስ አብዲሳ እና በብልጽግና ፓርቲ የክልሉ ቅርንጫፍ ጽህፈት ቤት ሃላፊ አቶ ፍቃዱ ተሰማ በተገኙበት ነው እየተካሄደ የሚገኘው።

በውይይቱ ላይ የክልሉ ርዕሰ መስተዳድር ጽህፈት ቤት ሃላፊ አብዱልአዚዝ ዳውድ(ዶ/ር) ÷ከለውጡ በኋላ በክልሉ የተመዘገቡ ውጤቶች ላይ ያተኮረ የውይይት መነሻ ሀሳብ ማቅረባቸውን ኢዜአ ዘግቧል፡፡

በዚህም የክልሉ መንግስት የተለያዩ ፈተናዎችን ተቋቁሞ ህዝቡን ተጠቃሚ የሚያደርጉ የልማት ስራዎች እያከናወነ መሆኑን ጠቅሰዋል።የፖለቲካ ፓርቲዎቹ በክልሉ እየተከናወኑ የሚገኙ የልማት ስራዎችን ሲጎበኙ መቆየታቸው ተመላክቷል፡፡