አዲስ አበባ፣ ግንቦት 25፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ከሲስተም ማሻሻያ ሥራ ጋር በተገናኘ በተፈጠረ ችግር ምክንያት ያለአግባብ ተወስዶ ከነበረው 801 ነጥብ 4 ሚሊየን ብር ውስጥ 98 ነጥብ 9 በመቶ ወይም 792 ነጥብ 71 ሚሊየን ብር የሚሆነውን ማስመለስ መቻሉን ገለፀ፡፡
ቀሪውን ገንዘብ የማስመለስ ሥራው መቀጠሉንም ባንኩ ገልጿል፡፡
መጋቢት 7 ቀን 2016 ዓ.ም ከሲስተም ማሻሻያ ሥራ ጋር በተገናኘ ባጋጠመ ችግር ምክንያት 801 ነጥብ 4 ሚሊየን ብር ያለአግባብ መወሰዱ ይታወሳል፡፡