የሀገር ውስጥ ዜና

ሚኒስቴሩ የ12ኛ ክፍል ሃገር አቀፍ ማጠቃለያ ፈተናን በተመለከተ ማብራሪያ ሰጠ

By Amele Demsew

June 02, 2024

አዲስ አበባ፣ ግንቦት 25፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ)የትምህርት ሚኒስቴር በበይነ መረብ (Online) የሚሰጠውን የ12ኛ ክፍል ሃገር አቀፍ ማጠቃለያ ፈተና በተመለከተ ማብራሪያ ሰጥቷል፡፡

ለመጀመሪያ ጊዜ በበይነ መረብ የሚሰጠውን የ12ኛ ክፍል ማጠቃለያ አገር አቀፍ ፈተና ወረቀት አልባ በማድረግ የዲጂታል ጉዞውን አንድ ምዕራፍ መጀመሩን ገልጿል፡፡

ይህንንም ጉዞ የተሳካ ለማድረግ በርካታ ስራዎች እየተሰሩ እንደሚገኙም አስታውቋል፡፡

ለተፈታኞች በክላስተር የተዘጋጀው ማስፈንጠሪያ (URL) ከፈተናው በፊት ገብተው የሚለማመዱበት ሲሆን የፈተናው እለት ደግሞ መፈተኛ መሆኑ ተገልጿል።

ስለሆነም ተፈታኞች ከዚህ በታች በሚፈተኑበት የፈተና ክላስተር ፊትለፊት በተቀመጠው ማስፈንጠሪያ በመግባት መለማምድ እንደሚችሉ አስታውቋል፡፡

እስካሁን username እና password ያለገኘ ተፈታኝ ካለ፣ ከዚህ በፊት ለትምህርት ቢሮዎች ስለተላከ፣ ከየትምህርት ቤቱ አስተባባሪዎች ማግኘት የሚችሉ መሆኑን ጠቁሟል፡፡