Site icon Welcome to Fana Broadcasting Corporate S.C

በኦሮሚያ የሚንቀሳቀሱ የፖለቲካ ፓርቲዎች በክልሉ ለሚከናወኑ የልማት ሥራዎች ድጋፋቸውን እንደሚቀጥሉ ገለጹ

አዲስ አበባ፣ ግንቦት 24፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) በኦሮሚያ ክልል ለሚከናወኑ የልማት ሥራዎች ድጋፋቸውን አጠናክረው እንደሚቀጥሉ በክልሉ የሚንቀሳቀሱ የፖለቲካ ፓርቲዎች የጋራ ምክር ቤት አባላት ገለጹ፡፡

አባላቱ በክልሉ በተለያዩ አካባቢዎች በግብርና፣ በትምህርት፣ በስራ ዕድል ፈጠራ፣ በጤና፣ በማኅበራዊ ልማት እየተከናወኑ ያሉ ስራዎችን እና የአገልግሎት መስጫ ተቋማትን ጎብኝተዋል፡፡

በምልከታቸውም በተግባር የክልሉን ሕዝብ ተጠቃሚነት የሚያረጋግጡ የልማት ሥራዎች መከናወናቸውን አረጋግጠናል ሲሉ ለፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬት ተናግረዋል፡፡

መሬት ላይ ካለው ተጨባጭ እውነታ በተለየ በሚቀርቡ አሉባልታዎች የተሳሳተ አረዳድ ይዘው መቆየታቸውን አስታውሰው÷ ጉብኝታቸውም ይህን ግንዛቤያቸውን እንደቀየረላቸው ገልጸዋል፡፡

በክልሉ እየተከናወኑ ያሉ የልማት ሥራዎች አበረታች መሆናቸውን በመግለጽ÷ በይበልጥ ተጠናክረው እንዲቀጥሉ እና ለዚህም የሚጠበቅባቸውን ድጋፍ እንደሚያደርጉ አረጋግጠዋል፡፡

በመራኦል ከድር

Exit mobile version