አዲስ አበባ፣ ግንቦት 24፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) ዛሬ በተካሄዱ ሦስት ዙር በረራዎች በሳዑዲ ዓረቢያ በአስቸጋሪ ሁኔታ ውስጥ የነበሩ 1 ሺህ 132 ኢትዮጵያውያን ወደ ሀገራቸው መመለሳቸውን የሴቶችና ማኅበራዊ ጉዳይ ሚኒስቴር አስታወቀ፡፡
ለተመላሽ ወገኖችም ተገቢውን ድጋፍ በማድረግ ከቤተሰብ ጋር የመቀላቀል ስራ እየተሰራ መሆኑ ተገልጿል፡፡
ከሚያዝያ 4 ቀን 2016 ዓ.ም ጀምሮ እየተከናወነ በሚገኘው ዜጎችን ወደ ኢትዮጵያ የመመለስ ሥራ ከ35 ሺህ በላይ ወገኖች መመለሳቸውን የሚኒስቴሩ መረጃ አመላክቷል።