የሀገር ውስጥ ዜና

በኮምቦልቻ ከተማ የ #ጽዱኢትዮጵያ ንቅናቄ አካል የሆነ የጽዳት ሥራ ተካሄደ

By Tamrat Bishaw

June 01, 2024

አዲስ አበባ፣ ግንቦት 24፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) የ  ሀገራዊ ንቅናቄ አካል የሆነ የጽዳት ሥራ “ፅዱ ከተሞች ለኢትዮጵያ ከፍታ” በሚል መሪ ሐሳብ በኮምቦልቻ ከተማ ተካሂዷል፡፡

በምክትል ርዕሰ መሥተዳድር ማዕረግ የከተማ ልማት ክላስተር አስተባባሪና የአማራ ክልል የከተማና መሠረተ ልማት ቢሮ ኃላፊ አሕመዲን መሐመድ (ዶ/ር) በዚሁ ወቅት እንዳሉት÷ ጽዱ ከተሞች እንፍጠር ተብሎ እንደ ሀገር ንቅናቄው የተጀመረው ከተሞች ለነዋሪዎችም ሆነ ለጎብኝዎች ምቹ እንዲሆኑ በማሰብ ነው።

በቀጣይም ሕዝብን በማሳተፍ፣ የአሠራር ሥርዓትን በመዘርጋት እና የባለ ድርሻ አካላትን ቅንጅታዊ አሠራር በማጎልበት ዘላቂነት ያለው አረንጓዴ ከተሞችን መፍጠር እንደሚገባ አስገንዝበዋል፡፡

የኮምቦልቻ ከተማ አሥተዳደር ምክትል ከንቲባ ወንድወሰን ልሳነ ወርቅ በበኩላቸው÷ ኮምቦልቻን ውብና ተመራጭ የኢንቨስትመንት መዳረሻ ለማድረግ እየተሰራ መሆኑን አስታውቀዋል፡፡

የ  ንቅናቄ ለከተሞች የቅንጦት ተግባር ሳይሆን መሠረታዊ ጉዳይ ነው ብለዋል፡፡