አዲስ አበባ፣ ግንቦት 23፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) የኢትዮጵያ አየር መንገድ ከአዲስ አበባ ሴራሊዮን ፍሪታወን የሚያደርገውን ቀጥታ በረራ በይፋ ጀምሯል፡፡
አየር መንገዱ ወደ ፍሪታወን በሳምንት 3 ጊዜ በረራ እንደሚያደርግ ተገልጿል።
በበረራ ማስጀመሪያ መርሃ ግብሩ ወቅት የኢትዮጵያ አየርመንገድ ግሩፕ ዋና ስራ አስፈጻሚ መስፍን ጣሰው እንደገለጹት÷ የአዲስ አበባ ፍሪታወን ቀጥታ በረራ አፍሪካን በአየር ትራንስፖርት የማስተሳሰሩ ስራ ተጠናክሮ መቀጠሉን ያሳያል ብለዋል፡፡
በረራው መጀመሩ በኢትዮጵያና በሴራሊዮን መካከል የነበረውን ሁለንተናዊ ግንኙነት ይበልጥ እንደሚያጠናክርም ገልጸዋል።
በኢትዮጵያ የሴራሊዮን አምባሳደር ሀሮልድ ቡንዱ ሳፋ በበኩላቸው÷ የኢትዮጵያ አየር መንገድ መዳረሻዎቹን በማስፋት አፍሪካውያንን ለማስተሳሰር የሚያደርገውን ጥረት አድንቀዋል።
በኃይለየሱስ ስዩም