Site icon Welcome to Fana Broadcasting Corporate S.C

አቶ ደስታ ሌዳሞ ኢንተርፕራይዞችን ለማበረታታት ያለመ ጉብኝት እያደረጉ ነው

አዲስ አበባ፣ ግንቦት 23፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) የሲዳማ ክልል ርዕሰ መሥተዳድር ደስታ ሌዳሞ በክልሉ በሥራ ላይ ያሉ ኢንተርፕራይዞችን ለማበረታታት እና የቀጣይ አቅጣጫ ለማስቀመጥ ያለመ ጉብኝት እያደረጉ ነው፡፡

በጉብኝታቸውም በሀዌላ ወረዳ ኑሬ ዱላቻ ቀበሌ የሚገኙ በወተት ላሞች ዕርባታ አርአያ የሆኑ ኢንተርፕራይዞችን ተመልክተዋል፡፡

በቀጣይም ሸበዲኖና ዳሌ ወረዳዎችን ጨምሮ በይርጋዓለምና ሌሎች ከተሞች የልማት እንቅስቃሴዎችን እንደሚጎበኙ መመላከቱን ኢዜአ ዘግቧል።

Exit mobile version