Site icon Welcome to Fana Broadcasting Corporate S.C

ሐጎስ ገብረህይወት በ5 ሺህ ሜትር የሩጫ ውድድር አሸነፈ

አዲስ አበባ፣ ግንቦት 22፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) ኢትዮጵያዊው አትሌት ሐጎስ ገብረህይወት በዳይመንድ ሊግ የ5 ሺህ ሜትር የወንዶች ሩጫ ውድድር አሸንፏል፡፡

በውድድሩ 12፡36፡73 ሰዓት በመግባት ሲያሸንፍ ፥ በ5ሺህ ሜትር ሩጫ ውድድር ሪከርድ ለመስበር በሁለት ሰከንድ ዘግይቶ መግባቱ ተገልጿል፡፡

አትሌቱ በተሳተፈበት በዚህ ውድድርም በታሪክ የምንጊዜም ሁለተኛውን ፈጣን ሰዓት ማስመዝገቡን ከዓለም አትሌቲክስ ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡

Exit mobile version