የሀገር ውስጥ ዜና

1 ሺህ 174 ኢትዮጵያውያን ከሳዑዲ ወደ ሀገራቸው ተመለሱ

By ዮሐንስ ደርበው

May 29, 2024

አዲስ አበባ፣ ግንቦት 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) በሶስት ዙር በተከናወነ በረራ በሳዑዲ አረቢያ በችግር ውስጥ የነበሩ 1 ሺህ 174 ኢትዮጵያውያን ወደ ሀገራቸው መመለሳቸውን የሴቶችና ማህበራዊ ጉዳይ ሚኒስቴር ገለጸ። በዛሬው እለት ወደ ሀገር ከተመለሱት መካከል እድሜያቸው ከ18 ዓመት በታች የሆኑ ሰባት ታዳጊዎች እንደሚገኙበት የሚኒስቴሩ መረጃ አመልክቷል።

ለተመላሽ ዜጎች በአየር ማረፊያና በማቆያ ማዕከላት ተገቢውን ድጋፍ እና እንክብካቤ በማድረግ ከቤተሰብ ጋር የመቀላቀል ስራ እየተሰራ እንደሚገኝ ተገልጿል።

ከሚያዚያ 4 ቀን 2016 ዓ.ም ጀምሮ እየተከናወነ በሚገኘው ዜጎችን ወደ ሀገር የመመለስ ስራ እስካሁን ከ32 ሺህ 800 በላይ ኢትዮጵያውያንን መመለስ መቻሉ ታውቋል።