አዲስ አበባ፣ ግንቦት 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) ቱርክ ከሚገኝ የትጥቅ አምራች ድርጅት ጋር በመተባበር “ሀገሬ” የተሰኘ የራሱን ብራንድ ማስተዋወቁን የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን አስታወቀ፡፡
የፌዴሬሽኑ ፕሬዚዳንት ኢሳያስ ጂራ እንደገለጹት÷ ፌዴሬሽኑ ከተቋሙ ጋር ያደረገው የመግዛት እና የመሸጥ ስምምነት የጊዜ ገደብ የለውም፡፡
ፌዴሬሽኑ ያስተዋወቀው የትጥቅ ብራንድ በኢትዮጵያ አዕምሯዊ ንብረት ባለስልጣን መመዝገቡን ተናግረዋል፡፡
የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን አዲሱን የትጥቅ ብራንድ በዓለም ዋንጫ ማጣሪያ ከጊኒ ቢሳው እና ጅቡቲ ጋር በሚያደርገው ጨዋታ ለመጀመሪያ ጊዜ እንደሚጠቀመው ገልጸዋል፡፡
በተጨማሪም ፌደሬሽኑ በፓኪስታን የተሠራ የመጫወቻ ኳስ አስተዋውቋል።
በወርቅነህ ጋሻሁን