አዲስ አበባ፣ ግንቦት 21፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) የጀርመኑ ክለብ ባየር ሙኒክ ቤልጂየማዊውን ቪንሴንት ኮምፓኒን በአሰልጣኝነት መሾሙን አስታውቋል፡፡
ኮምፓኒ ባየር ሙኒክን በኃላፊነት የተረከበው የቀድሞው የቡድኑ አሰልጣኝ ቶማስ ቱሄል መሰናበቱን ተከትሎ ነው፡፡
በዚህም አሰልጣኝ ቪንሴንት ኮምፓኒ ባየር ሙኒክን ለሦስት የውድድር ዓመታት ለማሰልጠን እስከ 2027 የሚያቆየውን ውል መፈረሙን ቢቢሲ ዘግቧል፡፡
ኮምፓኒ ባለፈው ዓመት ወደ እንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ አድጎ ዘንድሮ ወደሻምፒየንሽፕ የወረደውን በርንሌይን ሲያሰለጥን መቆየቱ ይታወሳል፡፡