አዲስ አበባ፣ ግንቦት 21፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) የፓኪስታን ባለሀብቶች በኢትዮጵያ በተለያዩ ኢንዱስትሪ ፓርኮች በመድኃኒት እና ጨርቃጨርቅ ዘርፎች ለመሠማራት እንደሚፈልጉ አስታወቁ፡፡
ከ80 በላይ የፓኪስታን ባለሀብቶችን ያካተተ ልዑክ የቂሊንጦ፣ ቦሌ ለሚ እና አዳማ ኢንዱስትሪ ፓርኮችን የሥራ እንቅስቃሴና መሠረተ-ልማቶች ጎብኝቷል፡፡
በጉብኝቱም በመድኃኒት፣ ጨርቃጨርቅ እንዲሁም ሌሎች የቴክኖሎጂ ምርቶችና የኢንቨስትመንት ዘርፎች ለመሰማራት እንደሚፈልግ ማሳወቁን የኮርፖሬሽኑ መረጃ አመላክቷል፡፡