Site icon Welcome to Fana Broadcasting Corporate S.C

ከንቲባ አዳነች ከመላው የመዲናዋ አመራሮች ጋር ተወያዩ

 

አዲስ አበባ፣ ግንቦት 20፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) የአዲስ አበባ ከተማ ከንቲባ አዳነች አቤቤ ከመላው የከተማዋ አመራሮች ጋር ተወያይተዋል።

ይህን ተከትሎ ከንቲባዋ በማህበራዊ ትስስር ገፃቸው÷ “ልመና እና ተረጂነትን ማስቀረት፣ የስራ እድልን በስፋት መፍጠር እና የኑሮ ውድነት ጫናን በዘላቂነት መቀነስ አንዱ ትልቅ ትኩረት የሚሰጠው ስራ በመሆኑ በዚሁ ላይ ከመላው የከተማችን አመራሮች ጋር ተወያይተናል” ብለዋል።

“ይህን ለማሳካት የልማት ሃይላችንን በማስተባበር እና ጸጋዎቻችንን በመጠቀም የጀመርናቸውን ስራዎች አጠናክረን በመቀጠል፣ ግንዛቤዎችን ከፍ በማድረግ እንዲሁም የስራዎቻችንን ውጤታማነት በማስቀጠል የምግብ ዋስትና ሉዓላዊነታችንን በማረጋገጥ ለብልፅግናችን እንተጋለን” ሲሉም ገልጸዋል።

Exit mobile version