አዲስ አበባ፣ ግንቦት 20፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) በቦሌ ለሚ እና በቂሊንጦ ኢንዱስትሪ ፓርኮች ያሉት ዝርዝር የኢንቨስትመንት አማራጮችና የመሰረተ-ልማት አቅርቦቶች ሳቢ መሆናቸውን የፓኪስታን ከፍተኛ የኢንቨስትመንት ልዑክ ገለጸ፡፡
ከ80 በላይ አባላትን ያየዛው የፓኪስታን ከፍተኛ የኢንቨስትመንት ልዑክ በፓኪስታን የኢትዮጵያ አምባሳደር ጀማል በክሪ ጋር በመሆን የቦሌ ለሚ እና ቂሊንጦ ኢንዱስትሪ ፓርክ የሥራ እንቅስቃሴን ገብኝቷል፡፡
በጉብኝታቸውም የልዑኩ አባላት በሰጡት አስተያየት ፓርኮቹ ያላቸው የተሟላ መሰረተ-ልማት ለኢንቨስትመንት ምቹና ሳቢ ነው ማለታቸውን የኢንዱስትሪ ፓርኮች ልማት ኮርፖሬሽን መረጃ አመላክቷል፡፡
በቀጣይ በየዘርፎቹ ያሉ የኢንቨስትመንት አማራጮችን ለይተው ለኢንቨስትመንት ዝግጁ የመሆን ሥራዎችን እንደሚያከናውኑም አሳውቀዋል፡፡