ዓለምአቀፋዊ ዜና

ቻይና በቀይ ባሕር በሚያልፉ የንግድ መርከቦች ላይ የሚደርሰው ጥቃት እንዲያበቃ ጠየቀች

By Tamrat Bishaw

May 28, 2024

አዲስ አበባ፣ ግንቦት 20፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) በቀይ ባሕር በሚጓጓዙ የንግድ መርከቦች ላይ የሚደርሰው ጥቃት አብቅቶ ሰላማዊ ጉዞ እንዲኖር የቻይና የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ዋንግ ዪ ጥሪ አቅርበዋል።

ሚኒስትሩ ጥሪውን ያቀረቡት በዛሬው ዕለት ከየመን የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ጋር በቻይና ቤጂንግ በተወያዩበት ወቅት ነው፡፡

በጉዳዩ ላይም ቻይና ገንቢ ሚናዋን ለመወጣት ዝግጁ መሆኗ መገለጹን ተቅሶ ሬውተርስ ዘግቧል።