Site icon Welcome to Fana Broadcasting Corporate S.C

ኢትዮጵያ በዓለም የጤና ጉባዔ ላይ እየተሳተፈች ነው

አዲስ አበባ፣ ግንቦት 19፣ 2016 (ኤፍ ቢሲ) 77ኛው የዓለም ጤና ጉባዔ በስዊዘርላንድ ጀኔቫ በዛሬው ዕለት መካሄድ ጀምሯል፡፡

“ሁሉም ለጤና፣ ጤና ለሁሉም” በሚል መሪ ሃሳብ እየተካሄደ በሚገኘው ጉባዔ ላይ ከ190 በላይ አባል ሀገራት ተወካዮችና ሌሎች አካላት ተሳትፈዋል፡፡

በጤና ሚኒስትር ዶ/ር መቅደስ ዳባ የተመራ የኢትዮጵያ ልዑክም በጉባዔው ላይ እየተሳተፈ መሆኑን የሚኒስቴሩ መረጃ ያመላክታል፡፡

በተለያዩ ዓለም አቀፍ የጤና አጀንዳዎች ላይ የሚመክረው ጉባዔው እስከ ግንቦት 24 ቀን 2016 ዓ.ም እንደሚካሄድ ተጠቁሟል፡፡

Exit mobile version