የሀገር ውስጥ ዜና

ቦይንግ ኩባንያ የአፍሪካ ዋና ጽሕፈት ቤቱን በአዲስ አበባ ሊከፍት ነው

By Melaku Gedif

May 27, 2024

አዲስ አበባ፣ ግንቦት 19፣ 2016 (ኤፍ ቢሲ) ግዙፉ የአሜሪካ አውሮፕላን አምራች ኩባንያ ቦይንግ የአፍሪካ ዋና ጽሕፈት ቤቱን በአዲስ አበባ ሊከፍት መሆኑን አስታውቋል፡፡

ኢትዮጵያ በደቡብ አፍሪካ ጁሃንስበርግ ከፈረንጆቹ ግንቦት 21 እስከ 23 ቀን በተካሄደው የአፍሪካ የአቪዬሽን ጉባዔ ላይ ተሳትፋለች፡፡

በጉበዔው ላይ ኩባንያው በሚቀጥለው ዓመት ቢሮውን በአዲስ አበባ ለመክፈት ማቀዱን አስታውቋል፡፡

የኢትዮጵያ አየር መንገድ ባለፈው መጋቢት ወር በአፍሪካ የመጀመሪያ ሞዴል የሆኑትን 8 ቦይንግ 777-9 አውሮፕላኖችን ለመግዛት ስምምነት ላይ መድረሱ ተመላክቷል፡፤

ባሳለፍነው ሕዳር ወር የኢትዮጵያ አየር መንገድ በአፍሪካ የአቪዬሽን ታሪክ ትልቅ የተባለለትን 67 ቦይንግ ጀት አውሮፕላኖች የግዢ ሥምምነት መፈረሙም የሚታወስ ነው፡፡