አዲስ አበባ፣ ግንቦት 19፣ 2016 (ኤፍ ቢሲ) በአማራ ክልል የግብይት ሥርዓቱን ለማሻሻል እና የኑሮ ውድነቱን ለማረጋጋት 1 ነጥብ 1 ቢሊየን ብር ለሸማች ማህበራትና ዩኒየኖች መሰራጨቱ ተገልጿል፡፡
የአማራ ክልል ንግድና ገበያ ልማት ቢሮ ከባለ ድርሻ አካላት ጋር የ10 ወራት አፈፃፀም ግምገማ መድረክ እያካሄደ ነው።
በመድረኩ የኑሮ ውድነቱን ለማረጋጋት ባለፉት 10 ወራት 478 ሺህ ኩንታል የሰብል ምርት እንዲሁም የተለያዩ የኢንዱስትሪ ምርቶች ለማህበረሰቡ መቅረባቸውን ተጠቅሷል፡፡
የቢሮው ሃላፊ ኢብራሒም መሃመድ (ዶ/ር) እንደተናገሩት÷ ኑሮን ለማረጋጋት የሸማች ህብረት ሥራ ማህበራት እና ዩኒየኖችን የመሸመት አቅም ለማሳደግ 1 ነጥብ 1 ቢሊየን ብር ተሰራጭቷል።
ከዚህ ውስጥም 678 ሚሊየን የሚሆነው ብር በተዘዋዋሪ ብድር የቀረበ መሆኑን ነው ያመላከቱት፡፡
ሕገ-ወጥ የንግድ ሥርዓትን ከመቆጣጠር አንጻርም 47 ሺህ ኩንታል የሰብል ምርትና በርካታ የኢንዱስትሪ ምርቶች በቁጥጥር ስር መዋላቸውን አንስተዋል፡፡
በእሸቱ ወ/ሚካኤል