የሀገር ውስጥ ዜና

በአዲስ አበባ የኮሮና ቫይረስ የተገኘባቸው ሰዎች ቁጥር 2 ሺህ 368 ደረሰ

By Tibebu Kebede

June 13, 2020

አዲስ አበባ ፣ ሰኔ 6 ፣ 2012 (ኤፍ ቢ ሲ) በአዲስ አበባ በ24 ሰዓታት ውስጥ በተደረገ የላብራቶሪ ምርመራ 232 ሰዎች ቫይረሱ ተገኝቶባቸዋል።

በዚህም በከተማዋ ቫይረሱ የተገኘባቸው ሰዎች ቁጥር 2 ሺህ 368 መድረሱን ነው የከተማ አስተዳደር ጤና ቢሮ ሪፓርት ያመለከተው።