የሀገር ውስጥ ዜና

በመዲናዋ በአፈር መደርመስ አደጋ የአንድ ወጣት ህይዎት አለፈ

By Amele Demsew

May 23, 2024

አዲስ አበባ፣ ግንቦት 15፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) በአዲስ አበባ ቦሌ ክ/ከተማ በግንባታ ላይ ከነበረ ህንጻ አጠገብ ያለ ቤት ውሃልክ ተደርምሶ የአንድ ወጣት ህይዎት ማለፉን የእሳትና አደጋ ስጋት ስራ አመራር ኮሚሽን ገለጸ፡፡

አደጋው ቦሌ ክፍለ ከተማ ወረዳ 7 በተለምዶ የረር ጉሊት ተብሎ በሚጠራ አካባቢ በግንባታ ስራ ላይ የነበሩ ሰራተኞች ላይ ከአጠገቡ ዳገት ላይ የነበረ የግለሰብ መኖሪያ ቤት ውሃ ልክ በመደርመሱ የደረሰ ሲሆን ÷ በዚህም የ28 ዓመት ወጣት ህይዎት ማለፉን የኮሚሽኑ ህዝብ ግንኙነት ባለሙያ ንጋቱ ማሞ ገልጸዋል፡፡

አደጋው መፈጠሩ ከተሰማ ጀምሮ የኮሚሽኑ ሰራተኞች በአደጋው ጉዳት የደረሰባቸው ሁለት ሰራተኞችን ህይዎት ለመታደግ ከፍተኛ ርብርብ ማድረጋቸውንም አቶ ንጋቱ ለፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬት ተናግረዋል፡፡

በአመለወርቅ ደምሰው