Site icon Welcome to Fana Broadcasting Corporate S.C

የሳዑዲ ባለሃብቶች በኢትዮጵያ የሚያደርጉትን የኢንቨስትመንትና ንግድ ተሳትፎ እንዲያጠናክሩ ጥሪ ቀረበ

አዲስ አበባ፣ ግንቦት 15፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አምባሳደር ታዬ አፅቀስላሴ ከሳዑዲ አረቢያ የንግድ ምክር ቤት ሰብሳቢ ሀሰን ሙጂብ ኦል ህዋይዚ ጋር ተወያይተዋል፡፡

በውይይታቸውም፤ የሳዑዲ አረቢያ ባለሃብቶች በኢትዮጵያ እያደረጉት ያለውን የኢንቨስትመንት እና ንግድ ተሳትፎ አጠናክረው እንዲቀጥሉ አምባሳደር ታዬ አፅቀስላሴ ጥሪ አቅርበዋል።

ኢትዮጵያ በአሁኑ ወቅት የተለያዩ ሀገራት ባለሃብቶችን ለመሳብ ሰፊ የማሻሻያ ስራዎችን በመስራት ምቹ የኢንቨስትመንት ከባቢያዊ ሁኔታን እየፈጠረች እንደምትገኝ ገልፀው፤ በተፈጠረው ምቹ ሁኔታ የሳዑዲ አረቢያ ባለሃብቶች ተጠቃሚ እንዲሆኑ ጠይቀዋል።

የሳዑዲ የንግድ ምክር ቤት ሰብሳቢ ሀሰን ሙጂብ በበኩላቸው÷ የሳዑዲ ባለሃብቶች በኢትዮጵያ በኢንቨስትመንት እና ንግድ በተለይም በግብርና ምርቶች ማቀነባበር እና በማምረቻ ዘርፎች ለመሳተፍ ከፍተኛ ፍላጎት ያላቸው መሆኑን ገልፀዋል፡፡

የተመረጡ ባለሃብቶች በመጭው ነሐሴ ወር በኢትዮጵያ የቢዝነስ ጉብኝት እንደሚያደርጉ መግለጻቸውን ከውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ያገኘነው መረጃ ያመላክታል።

Exit mobile version