የሀገር ውስጥ ዜና

በሰብል የምንሸፍነው የመሬታችን ይዞታ ቀስ በቀስ እየጨመረ ነው – ጠ/ሚ ዐቢይ (ዶ/ር)

By Meseret Awoke

May 21, 2024

አዲስ አበባ፣ ግንቦት 13፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) በሰብል የምንሸፍነው የመሬታችን ይዞታም ቀስ በቀስ በመጨመር ላይ ይገኛል ሲሉ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ገለጹ፡፡

ጠቅላይ ሚኒስትሩ በማህበራዊ ትስስር ገጻቸው ባሰፈሩት ሃሳብ፥ ባለፉት ጥቂት ዓመታት ዋናውን የዝናብ ወቅት ምርት ሳናስተጓጉል የበጋ ስንዴ ልማት ጥረታችንን ለማስፋፋት ችለናል ብለዋል፡፡

የዛሬው ምልከታ የስራዎችን ቀጣይነት የተመለከትንበት ነበር በማለት ገልጸው፥ ግብርና ጠንካራ ኢንቨስትመንት እንሚፈልግም ነው ያነሱት፡፡

አክለውም፥ በሰብል የምንሸፍነው የመሬታችን ይዞታም ቀስ በቀስ በመጨመር ላይ ይገኛል ብለዋል።