Site icon Welcome to Fana Broadcasting Corporate S.C

በሁሉም የወለጋ ዞኖች ሰላም እየተረጋገጠ መምጣቱን የዳሎል ማዕከላዊ ዕዝ ገለጸ

አዲስ አበባ፣ ግንቦት 13፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) በአራቱ የወለጋ ዞኖች እየተከናወነ ባለው ሕግ የማስከበር ርምጃ በአካባቢው ሰላም እየተረጋገጠ መምጣቱን በሀገር መከላከያ ሰራዊት የዳሎል ማዕከላዊ ዕዝ ገለጸ።

ባለፉት ወራት በምሥራቅ፣ ምዕራብ፣ ቄለም እና ሆሮ ጉዱሩ ወለጋ ዞኖች በሽብር ቡድኑ ላይ በተወሰደ ርምጃ በርካታ አካባቢዎችን ነጻ ማድረግ መቻሉን በዕዙ የሥነ-ልቦና ግንባታ ኃላፊ ኮሎኔል ለቺሳ መገርሳ ገልጸዋል።

የሽብር ቡድኑ በአካባቢው በሕዝብ ላይ አፀያፊ ተግባራትን በመፈጸም ከባድ ውድመት ማድረሱን ለኢዜአ የተናገሩት ኃላፊው÷ የትምህርትና ኢኮኖሚያዊ እንቅስቃሴዎችን ጭምር ሲያውክ መቆየቱን አስታውሰዋል፡፡

አሁን ግን የመከላከያ ሰራዊት ከሌሎች የጸጥታ ኃይሎች ጋር ተቀናጅቶ እያከናወነ ባለው የሕግ ማስከበር ርምጃ በአካባቢው ሰላም እየተረጋገጠ መምጣቱን አስረድተዋል፡፡

Exit mobile version