አዲስ አበባ፣ ግንቦት 13፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) 6ኛው ሀገር አቀፍ የፖሊስ ምርምር ሲምፖዚየም በፖሊስ ዩኒቨርሲቲ እየተካሄደ ነው፡፡
የዩኒቨርሲቲው ፕሬዚዳንት ምክትል ኮሚሽነር ጀነራል መስፍን አበበ በዚሁ ጊዜ÷ በሲምፖዚየሙ የፖሊስ አገልግሎት ክፍተቶችን በጥናት ተመስርቶ ማመላከት የሚችሉና ጠቃሚ ሃሳቦች የሚነሱበት እንደሚሆን ገልፀዋል።
ዩኒቨርሲቲው ከአፍሪካ ተመራጭ ተቋም እንዲሆን ለማስቻል በርካታ የስልጠና ማዕከላት እየተገነቡ መሆኑንም ምክትል ኮሚሽነር ጀነራሉ አንስተዋል።
በሁሉም ፖሊሳዊ የምርመራ እና ፎረንሲክ አቅምን ማሳደግ የሚችሉ ስራዎችን እና የምርምር ስራዎችን በተጓዳኝ ለማስኬድ ስራዎች እየተከናወኑ ነው ብለዋል።
እነዚህ ሁሉ ሃሳቦችና ትልሞችንም እውን ለማድረግ በጥናትና ምርምር የተመሰረተ ተግባር ለማከናወን ባለሙያዎችን ማፍራት ወሳኙ እርምጃ እንደሆነ ተነግሯል።
የሲምፖዚየሙ አላማ የብዙ ባለሙያዎችን እውቀት መካፈል እና መረዳት ወሳኝ በመሆኑ እንደሆነም በመድረኩ ተመላክቷል።
በይስማው አደራው