አዲስ አበባ፣ ግንቦት 13፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) በጋምቤላ ክልል በበጀት ዓመቱ ዘጠኝ ወራት ከ1 ነጥብ 6 ቢሊየን ብር በላይ ገቢ መሰብሰቡን የክልሉ ገቢዎች ቢሮ አስታወቀ።
የቢሮው ኃላፊ አቶ ቱት ጆክ÷ በዘጠኝ ወራት 1 ቢሊየን 775 ሚሊየን 556 ሺህ ብር ገቢ ለመሰብሰብ ታቅዶ 1 ቢሊየን 626 ሚሊየን 785 ሺህ ብር ገቢ መሰብሰቡን ገልጸዋል።
የተሰበሰበው ገቢ ከባለፈው ዓመት ተመሳሳይ ወቅት ጋር ሲነፃፀር የ323 ሚሊየን 940 ሺህ ብር ብልጫ እንዳለው ጠቁመዋል።
በክልሉ ገቢ የመሰብሰብ ዓቅም ከጊዜ ወደ ጊዜ እያደገ መሆኑን የጠቆሙት አቶ ቱት፤ በቀጣይም ገቢን አሟጦ ለመሰብሰብ እየተሰሩ የሚገኙ ስራዎች ተጠናክረው ይቀጥላሉ ብለዋል።
በክልሉ በበጀት ዓመቱ ከ2 ነጥብ 3 ቢሊየን ብር በላይ ገቢ ለመሰብሰብ መታቀዱን ከክልሉ የመንግስት ኮሙኒኬሽን ጉዳዮች ጽህፈት ቤት ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡