Site icon Welcome to Fana Broadcasting Corporate S.C

በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል የሌማት ትሩፋት በአግባቡ እየተተገበረ መሆኑ ተገለጸ

አዲስ አበባ፣ ግንቦት 11፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል የሌማት ትሩፋት በልዩ ሁኔታ እየተተገበረ መሆኑን በምክትል ርዕሰ መሥተዳድር ማዕረግ የገጠር ክላስተር አስተባባሪና የግብርና ቢሮ ኃላፊ ኡስማን ሱሩር ገለጹ፡፡

የሌማት ትሩፋቱ ተቀዳሚ ዓላማ እያንዳንዱ ዜጋ የእንስሳት ተዋፅኦዎችን በቤቱ እንዲያገኝ እና ጤናው እንዲጠበቅ ማድረግ መሆኑንም ነው አቶ ኡስማን ያስረዱት፡፡

ለዚሁ ዓላማ መሳካት ይረዳ ዘንድም በክልሉ የሌማት ትሩፋት መንደሮች እየተፈጠሩ ነው ማለታቸውን የግብርና ሚኒስቴር መረጃ አመላክቷል፡፡

በዚህም የአትክልትና ፍራፍሬ ልማት የሌማት ትሩፋት አካል ሆኖ በትኩረት እየተሠራ መሆኑን ነው የገለጹት፡፡

Exit mobile version