ስፓርት

የ2023/24 የእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ ምሽቱን ፍጻሜውን ያገኛል

By Tamrat Bishaw

May 19, 2024

አዲስ አበባ፣ ግንቦት 11፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) የእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ የ2023/24 የውድድር ዘመን ዛሬ በተመሳሳይ አመሻሽ 12:00 ላይ በሚደረጉ ጨዋታዎች ይጠናቀቃል።

የሊጉ መሪ ማንቼስተር ሲቲ እና ተከታዩ አርሰናል ዋንጫውን የማሸነፍ ዕድል ይዘው በሜዳቸው ተጋጣሚዎቻቸውን ያስተናግዳሉ።

ማንቼስተር ሲቲዎች በኢቲሃድ ከዌስትሃም ጋር የሚያደርጉትን ጨዋታ በድል መቋጨት የሚችሉ ከሆነ፤ ለአራት ተከታታይ የውድድር ዓመታት የፕሪሚየር ሊጉን ዋንጫ በማሳካት አዲስ ታሪክ ይጽፋሉ።

ማንቼስተር ሲቲ የሚሸነፍ ወይም አቻ የሚያጠናቅቅ ከሆነ እና አርሰናል ኤቨርተንን ማሸነፍ ከቻለ የፕሪሚየር ሊጉ ባለ ክብር መሆኑን ያረጋግጣል።