ስፓርት

በፕሪሚየር ሊጉ አዳማ ከተማ ተጋጣሚውን አሸነፈ

By Tamrat Bishaw

May 19, 2024

አዲስ አበባ፣ ግንቦት 11፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) በ25ኛ ሣምንት የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ አዳማ ከተማ ሲዳማ ቡናን 2 ለ 1 ረትቷል፡፡

በጨዋታውም መስዑድ መሐመድ እና ቢንያም አይተን ለአዳማ ከተማ እንዲሁም ደስታ ዮሐንስ ለሲዳማ ቡና ጎሎቹን ከመረብ ማሳረፍ ችለዋል፡፡

እንዲሁም 12 ሠዓት ላይ በተካሄደ ጨዋታ ሻሸመኔ ከተማን ኢትዮጵያ ቡና 2 ለ 1 አሸንፏል፡፡

የሻሸመኔ ከተማን ጎል ሁዛፍ አሊ ሲያስቆጥር፤ የሲዳማ ቡናን ደግሞ በፍቃዱ ዓለማየሁ እና ራምኬል ጀምስ ማስቆጠር ችለዋል፡፡