አዲስ አበባ፣ ግንቦት10፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) በሦስት ዙር በረራ በተከናወነ በሳዑዲ አረቢያ በችግር ውስጥ የነበሩ ዜጎችን የመመለስ ስራ 1 ሺህ 147 ኢትዮጵያውያንን ወደ ሀገራቸው መመለስ ተችሏል።
በዛሬው ዕለት ወደ ሀገር ከተመለሱት 1 ሺህ 147 ዜጎች ውስጥ 1ሺህ 46ቱ ወንዶች፣ 80 ሴቶች እና 21 ጨቅላ ህፃናት መሆናቸው ተገልጿል፡፡
ለተመላሽ ዜጎች በአየር ማረፊያና በማቆያ ማዕከላት ተገቢውን ድጋፍ እና እንክብካቤ በማድረግ ከቤተሰብ ጋር የመቀላቀል ስራ እየተሰራ ይገኛል፡፡
ከሚያዝያ 4 ቀን 2016ዓ.ም ጀምሮ እየተከናወነ በሚገኘው ዜጎችን ወደ ሀገር የመመለስ ስራ ከ25 ሺህ 800 በላይ ኢትዮጵያውያንን መመለስ መቻሉን ከሴቶችና ማሕበራዊ ጉዳዮች ሚኒስቴር ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡