Site icon Welcome to Fana Broadcasting Corporate S.C

አሜሪካ ለጋዛ የሰብዓዊ ድጋፍ መግባቱን ማረጋገጧን አስታወቀች

አዲስ አበባ፣ ግንቦት 9፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) አሜሪካ ለጋዛ የሰብዓዊ ድጋፍ ተሽከርካሪዎች በጊዜያዊ ተንሳፋፊ የተሸከርካሪ ማቆሚያ ሥፍራ በኩል መግባታቸውን አረጋግጫለሁ ስትል ገልጻለች፡፡

2 ነጥብ 2 ሚሊየን የሚጠጉ ፍልስጤማውያን የምግብ፣ የመጠለያ እና ሌሎች እርዳታ እንደሚያስፈልጋቸውም ተገልጿል፡፡

እርዳታ በየብስ ወደ ጋዛ ማድረስ አደገኛ ስለሆነ ሌሎች አማራጮችን መጠቀም ግድ በመሆኑ ውሃ ላይ ጊዜያዊ የተሽከርካሪ እና የመርከብ ማቆሚያ በመገንባት ወደ ጋዛ እርዳታ ለማድረስ ነው የታቀደው፡፡

ይህን ተከትሎ አሁን ላይ አሜሪካ ድጋፉ በተፈለገበት ቦታ መድረሱን ማረጋገጠጧን ገልጻለች፡፡

በጋዛ ላሉ ንጹሃን ተጨማሪ እርዳታ በባህር ኮሪደር በኩል ለማድረስ ቀጣይነት ያለው ሁሉን አቀፍ ጥረት እየተደረገ መሆኑን አሜሪካ አሳውቃለች።

በሚቀጥሉት ቀናትም 500 ቶን የሚጠጋ የሰብዓዊ እርዳታ ወደ ጋዛ ይገባል ተብሎ ይጠበቃል ሲል የአሜሪካ ማዕከላዊ ዕዝ አስታውቋል።

ሆኖም ግን የተባበሩት መንግስታት ድርጅት (ተመድ) የባህር ኮሪደር ለሰብዓው እርዳታ ለማቅረብ ፈጣኑ እና ውጤታማ መንገድ እንዳልሆነ ገልጾ፤ አስጠንቅቋል፡፡

ባለፈው ሣምንት እስራኤል በራፋህ መሻገሪያ ላይ ያለውን የጋዛን ክፍል ከተቆጣጠረች በኋላ ለግዛቱ የሚደርሰው የእርዳታ አቅርቦት መቀነሱን ጠቅሶ የዘገበው ቢቢሲ ነው።

Exit mobile version