አዲስ አበባ፣ ግንቦት 9፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) ሰሜን ኮሪያ በዛሬው እለት በምስራቅ የባህር ዳርቻዋ ላይ በርካታ የአጭር ርቀት ተወንጫፊ ሚሳኤሎች ወደ ባህር መተኮሷን የደቡብ ኮሪያ ወታደራዊ ኃይል አስታወቀ።
የደቡብ ኮሪያ የጥምር ጦር ኃላፊዎች ሚሳኤሎቹ የተተኮሱት ከምስራቃዊ የባህር ጠረፍ ዎንሳን ከተማ ነው ማለታቸውን ዘገባዎች አመላክተዋል፡፡
መገናኛ ብዙሃኑ እንደገለጹት፤ የአጭር ርቀት ተወንጫፊ ሚሳኤል እንደተተኮሰ እና የውሀ አካል ላይ ወድቋል።
ቀደም ሲል የሰሜን ኮሪያ መሪ ኪም ጆንግ ኡን እህት ሀገሪቱ የጦር መሳሪያዎችን ወደ ውጭ ትልካለች የሚለውን አስተያየት በማጣጣል ታክቲካል መሳሪያዎቹ ደቡብ ኮሪያን ከጥቃት ለመከላከል ብቻ የታሰቡ ናቸው ማለታቸው ተገልጿል።
ሰሜን ኮሪያ የመከላከል አቅሟን የማሻሻል መርሀ ግብሯ አካል መሆኑን ለመግለፅ በቅርብ ወራት ውስጥ ባለስቲክ እና ክሩዝ ሚሳኤሎች እንዲሁም ታክቲካል ሮኬቶችን ማስወንጨፏንም ጠቁመዋል።
የአሜሪካ እና የደቡብ ኮሪያ ባለስልጣናት ሰሜን ኮሪያ የጦር መሳሪያዎችን ለሩሲያ ትልካለች በሚል ቢከሱም ሞስኮ እና ፒዮንግያንግ በበኩላቸው ክሱን አጣጥለውታል፡፡