የሀገር ውስጥ ዜና

ወጣቱን ይዘን ለኢትዮጵያ ብልጽግና እንሠራለን – አቶ እንዳሻው ጣሰው

By Amele Demsew

May 17, 2024

አዲስ አበባ፣ ግንቦት 9፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) ወጣቱን ኃይል ከጎናችን አሠልፈን ለኢትዮጵያ ብልጽግና እንሠራለን ሲሉ የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ምክትል ርዕሰ መሥተዳድር እንዳሻው ጣሰው ገለጹ፡፡

ምክትል ርዕሰ መሥተዳድሩ ከሀድያ ዞን የተለያዩ መዋቅሮች ከተውጣጡ ከ1 ሺህ በላይ ወጣቶች ጋር በሰላምና ልማት እንዲሁም በመልካም አሥተዳደር ጉዳዮች ላይ በሆሳዕና ከተማ እየተወያዩ ነው፡፡

አቶ እንዳሻው በውይይቱ ላይ ባደረጉት ንግግርም ወጣቱን ኃይል ከጎናችን አሠልፈን ለኢትዮጵያ ብልጽግና እንሠራለን ብለዋል፡፡

የክልሉ መንግሥት ከወጣቶቹ ጋር ለመወያየት ላሳየው ተነሳሽነትም የዞኑ ዋና አሥተዳዳሪ ማቴዎስ አኒዮ አመስግነዋል፡፡

ከጉራጌ ዞንና ቀቤና ልዩ ወረዳ ወጣቶች ጋርም ቀደም ሲል ተመሳሳይ ውይይቶች መካሄዳቸውን የክልሉ ኮሙኒኬሽን መረጃ አመላክቷል፡፡