Site icon Welcome to Fana Broadcasting Corporate S.C

ም/ጠ/ሚ ተመስገን ጥሩነህ ከአዘርባጃን ጠቅላይ ሚኒስትር ጋር መከሩ

 

አዲስ አበባ፣ ግንቦት 8፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ)ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ተመስገን ጥሩነህ ከአዘርባጃን ጠቅላይ ሚኒስትር አሊ አሳዶቭ ጋር ተወያዩ፡፡

በውይይታቸው÷ ኢትዮጵያና አዘርባጃን በንግድ፣ በኢንቨስትመንት፣ በቴክኖሎጂ እና በሌሎች ዘርፎቸያላቸውን ትብብር የበለጠ ማሳደግ እና በጋራ መስራት በሚችሉባቸው ጉዳዮች ዙሪያ መክረዋል።

ምክክሩን አስመልክቶ ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትሩ በማህበራዊ ትስስር ገፃቸው “ምክክራችን እጅግ ውጤታማ የነበረ ሲሆን የሁለቱን ሀገሮች ህዝብ ዕድገት እና ብልፅግና በመደጋገፍ እና በትብብር መንፈስ ለመስራት ተስማምተናል” ብለዋል፡፡

 

Exit mobile version