የሀገር ውስጥ ዜና

ኢትዮጵያና አዘርባጃን የፀጥታና ደኅንነት ዘርፎችን ጨምሮ በተለያዩ ጉዳዮች በጋራ ለመሥራት ተስማሙ

By ዮሐንስ ደርበው

May 15, 2024

አዲስ አበባ፣ ግንቦት 7፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) ኢትዮጵያ እና አዘርባጃን በመረጃ፣ የፀጥታና ደኅንነት ዘርፎች የጋራ ትብብር አቅም ግንባታና ሀገራቱን ተጠቃሚ በሚያደርጉ ሌሎች ፕሮጀክቶችን በጋራ ለመፈጸም ተስማሙ፡፡

ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ተመስገን ጥሩነህ ከአዘርባጃን የሀገር ውስጥ ጉዳዮች ሚኒስትር ኮሎኔል-ጀነራል ኢይቫዞቭ ቪላያት ሱለይማን ጋር ውጤታማ ውይይት ማድረጋቸውን አስታውቀዋል፡፡

በውይይታቸውም የደኅንነት ጉዳዮችን ጨምሮ የኢትዮጵያን እና አዘርባጃን የሁለትዮሽና የባለብዙ ወገን ትብብሮችን ለማጠናከር የሚያስችሉ የቀጣይ ስራዎች ላይ መክረናል ሲሉ በማኅበራዊ ትስስር ገጻቸው ገልጸዋል፡፡

እንዲሁም በመረጃ፣ የፀጥታና ደኅንነት ዘርፎች የጋራ ትብብር አቅም ግንባታና ሌሎች ጉዳዮች ሁለቱን ሀገራት ተጠቃሚ የሚያደርጉ ፕሮጀክቶችን በጋራ ለመፈጸም ተስማምተናል ነው ያሉት።