የሀገር ውስጥ ዜና

ም/ጠ/ሚ ተመስገን ጥሩነህ አዘርባጃን ገቡ

By Amele Demsew

May 14, 2024

አዲስ አበባ፣ ግንቦት 6፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ተመስገን ጥሩነህ አዘርባጃን ገብተዋል፡፡

ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትሩ የረጅም ጊዜ ወዳጅና አጋር ሀገር የሆነችው አዘርባጃን መግባታቸውን በማህበራዊ ትስስር ገጻቸው አስታውቀው፤ ለተደረገቸው ደማቅ አቀባበል ለሀገሪቱ መንግስት ምስጋና አቅርበዋል፡፡

በሀገሪቱ በሚኖራቸው ቆይታ በብዙ መስኮች የዘለቀውን ጠንካራ ግንኙነትና ትብብር ወደ ላቀ ደረጃ የሚያሻግሩ ምክክሮችና ስምምነቶች እንደሚያደርጉም ገልጸዋል፡፡