Site icon Welcome to Fana Broadcasting Corporate S.C

የ8100 A 3ኛ ዙር ዕጣ ወጣ

አዲስ አበባ፣ ሰኔ 5፣ 2012 (ኤፍ.ቢ.ሲ) ለታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ ግንባታ የሚውል ገቢ ለማሰባሰብ የሚካሄደው የ8100 A ዕጣ 3ኛ ዙር ዛሬ ወጣ።

በብሔራዊ ሎተሪ አዳራሽ በተካሄደ የዕጣ ማውጣት ስነ-ስርዓት አሸናፊው ቁጥር የ ኤስ ኤም ኤስ ቁጥር 084492978 ሆኖ ወጥቷል።

የዕጣው ሽልማት 2 ነጥብ 2 ሚሊዮን ብር የሚያወጣ ዘመናዊ ሃይሉክስ ፒክአፕ መኪና መሆኑን ኢዜአ ዘግቧል።

በስልክ መልዕክት የገቢ ማሰባሰቢያው የተጀመረው በዚህ ዓመት የካቲት ወር ላይ ሲሆን ለተጨማሪ ሶስት ወር የሚቆይ ይሆናል።

Exit mobile version